
የጋዜጣዊ መግለጫ ምንጮች
ስለመለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ – ከፍራንክሊን ግርሃም ጋር ለተሰኘው መርሐ ግብር ላሳዩት ፍላጎት እናመሰግናለን። የመርሐ ግብሩን ሽፋን ለመስጠት ከዚህ ገጽ ሊያገኙ የሚፈልጓቸውን መረጃዎች፥ የመርሐ ግብሩን ዝርዝር ጉዳይ፥ የሚዲያ አድራሻ መረጃ፥ ዳውንሎድ ልታድርጉ የምትችሏቸውን ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ፎቶ ግራፎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች እና ሌሎች ሊረዷችሁ የሚችሉ መረጃዎችን ከዚህ ገጽ ሊያገኙ ይችላሉ።
ጋዜጣዊ መለጫ
“መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ከፍራንክሊን ግርሃም ጋር” ለአዲስ አበባ የመጣ የተስፋና የእግዚአብሔር ፍቅር መልዕክት
አዲስአበባ፥ኢትዮጵያ፤ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም– የቢሊ ግራሃም የወንጌል ማኅበር በ1952 ዓ.ም ወንጌላዊ ቢሊግራሃም በአዲስ አበባ ስቴዲየም ወንጌል ከሰበኩና በንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ በቤተ መንግስታቸው በክብር ተጋብዘው ከተሸለሙ ከ 65 ዓመታት በኋላ የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ ለሚያደርገው ታሪካዊ የሁለት ቀናት መርሐ ግብር ለማከናወን ወደ አዲስ አበባ እየተመለሰ ይገኛል።
ከ1,600 በላይ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የወንጌላዊ ቢሊ ግርሃም ልጅ የሆኑትን ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግርሃምን በአዲስ አበባ እንዲሰብኩ በመጋበዝ ከቢሊ ግራሃም የወንጌል ማኅበር /ቢሊግርሃም ኢባንጀሊስቲክ አሶሴሽን/ ጋር በመተባበር ላይ ይገኛሉ። ልክ እንደ አባታቸው ፍራንክሊን ግራሃም ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥልቅ እና ታላቅ አክብሮት ያላቸው ሲሆን ላለፉት 40 አመታትም ወደዚህች ሀገር በተደጋጋሚ መጥተዋል።